🤖 OpenAI አዲሱን GPT-5.6 በሶስት ሞዴሎች ይፋ አደረገ! OpenAI Sol፣ Terra እና Luna የተባሉ ሶስት ሞዴሎችን ያካተተውን GPT-5.6 የተሰኘ አዲስ የAI ስሪት ይፋ አድርጓል። ዋና ዋና አዳዲስ ነገሮች፦ ከፍተኛ ብቃት በላቀ ፍጥነት፦ 'Sol' የተባለው ሞዴል በ"Agents' Last Exam" ፈተና ላይ 53.6 በማስመዝገብ፣ Claude Fable 5ን በ13.1 ነጥብ ብልጫ አሸንፏል። ይህን ያደረገው ደግሞ የClaudeን አንድ አራተኛ (1/4) ወጪ ብቻ በመጠቀም ነው። 'Terra' እና 'Luna' የተባሉት ሞዴሎችም በተመሳሳይ በጣም ባነሰ ወጪ Claude Fable 5ን ይበልጣሉ። የኮዲንግ ንጉስ፦ በኮዲንግ (Artificial Analysis Coding Agent index) 'Sol' 80.0 ነጥብ በማስመዝገብ የClaude Fable 5ን (77.2) በልጧል። ከግማሽ በታች 'tokens' የሚጠቀም ሲሆን፣ ፍጥነቱ ሁለት እጥፍ የላቀ እና ወጪውም በሲሶ (1/3) የቀነሰ ነው። Ultra Mode፦ ብዙ ኤጀንቶችን (agents) በአንድ ላይ ጎን ለጎን በማሰራት ስራዎችን እጅግ ፈጣን በሆነ መንገድ ያከናውናል። ራስን የማረም ብቃት (Visual Quality Control)፦ ጽሑፎችንና ኮዶችን አውጥቶ ከመስጠቱ በፊት የተሰሩ ስህተቶችን በራሱ አይቶ የማረም ልዩ ችሎታ አለው። በዚህም እጅግ ንጹህ እና ጥራት ያላቸውን ፕረዘንቴሽኖች፣ ሰነዶች እና ሰንጠረዦችን ከተለያዩ የ'Template' አማራጮች ጋር ያዘጋጃል። ChatGPT Work፦ አሁን በቀጥታ በራሱ ውስጥ እንደ 'Agent' ሆኖ ተካቶ ስራ ጀምሯል። SHARE 🚀 @technews_et @technews_et
https://t.me/technews_et/14119